የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ስለኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወጣው አዋጅ ቁጥር 1148/2011 በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሬጉላቶሪ ሥራዎች የሚውሉ የተለያዩ መመሪያዎችን በማርቀቅ የባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጥባቸው ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሠረት መመሪያዎቹ በአማርኛ ቋንቋ ተዘጋጅተው ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡባቸው ይፋ የተደረጉ መሆኑን እየገለጽን የአስተያየት መስጫ ጊዜ ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 5:59 የሚያበቃ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን

The Ethiopian Communications Authority wishes to provide an update relating to the recently-announced stakeholder consultation for three directives it drafted pursuant to its powers under the Communications Service Proclamation No. 1148/2019. The Authority has now made available the Amharic versions of these draft directives. Accordingly, the new date for the stakeholder consultation for submission of comments will start on June 1, 2020 and end on June 19, 2020 at 11:59 PM, East Africa Time.

The Ethiopian Communications Authority