Stakeholder Consultation on Safaricom Telecommunications Ethiopia’s Draft Consumer Right and Protection Code of Conduct

The Ethiopian Communications Authority, pursuant to Article 6 Sub-Article (14) of the Communications Service Proclamation No. 1148/2019, is mandated to safeguard the interest of Consumers of Communications Services. Article 50(3) of the Proclamation also provides that the Authority shall in particular require each Telecommunications Operator to establish a code of conduct that shall specify the rights of Consumers including the Consumer’s right to lodge a complaint with Telecommunications Operator or with the Authority.

In addition to the provisions of the proclamation, Article 5 and 6 of Telecommunications Consumer Rights and Protection Directive No. 832/2021 obliges Licensees to establish the Code of Conduct and submit to the Authority for Approval through stakeholder consultation in accordance with Article 50(4) of the Proclamation. Accordingly, Safaricom Telecommunications Ethiopia PLC has submitted its Draft Consumer Rights and Protection Code of Conduct to the Authority for Approval.

Therefore, the Ethiopian Communications Authority announces a call for stakeholder consultation on the Draft Consumer Rights and Protection Code of Conduct developed by Safaricom Telecommunications Ethiopia PLC to collect contributions or opinions on the Draft Code of Conduct.

This Stakeholder Consultation will start on December 20, 2022, and will run until January 9,2023.

All contributions from relevant stakeholders are welcome, and stakeholders who wish to comment on the Draft Code of Conduct can address their comments to the Authority via e-mail to the address consultation@eca.et.

The Ethiopian Communications Authority

DRAFT CONSUMER RIGHTS AND PROTECTION CODE OF CONDUCT-ENG

 

በሳፋሪኮም ቴሌኮሚዩኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ረቂቅ የተጠቃሚዎች መብት እና ጥበቃ የሥምግባር ደንብ ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክር

የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን በኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 1148/2011 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ (14) መሠረት የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ተጠቃሚዎችን መብት የማስጠበቅ ሥልጣን ተሰጥቶታል። የአዋጁ አንቀጽ 50(3) ባለሥልጣኑ በተለይ እያንዳንዱ የቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተር ተጠቃሚዎች ለኦፕሬተሩ ወይም ለባለሥልጣኑ ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉበትን ሥርዓት ጨምሮ የተጠቃሚዎችን መብት የሚደነግግ የሥነ-ምግባር ደንብ እንዲያዘጋጅ መጠየቅ እንደሚችል ይደነግጋል።

በአዋጁ ከተደነገገው በተጨማሪ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ተጠቃሚዎች መብትና ጥበቃ መመሪያ ቁጥር 832/2013 አንቀጽ 5 እና 6 ባለፈቃዶች የሥነ-ምግባር ደንብ በማዘጋጀት በአዋጁ አንቀጽ 50(4) መሠረት የባለድርሻ አካላት ምክክር ተካሂዶበት እንዲጸድቅ ለባለሥልጣኑ እንዲያቀርቡ ያስገድዳል። በዚህም መሠረት ሳፋሪኮም ቴሌኮሚዩኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ ያዘጋጀውን ረቂቅ የተጠቃሚዎች መብት እና ጥበቃ የሥነ-ምግባር ደንብ እንዲፀድቅለት ለባለሥልጣኑ አቅርቧል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን በሣፋሪኮም ቴሌኮሚዩኒኬሽንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ በተዘጋጀው ረቂቅ የተጠቃሚዎች መብትና ጥበቃ የሥነ- ምግባር ደንብ ላይ ከባለድርሻ አካላት አስተያየቶችን ለማሰባሰብ የባለድርሻ አካላት የምክክር ጥሪ ያስተላልፋል።

ይህ የባለድርሻ አካላት ምክክር ከታህሳስ 11 ቀን 2015 ጀምሮ እስከ ጥር 1 ቀን 2015 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስተያየቶች እንዲቀርቡ የምናበረታታ ሲሆን በረቂቅ የሥነ-ምግባር ደንቡ ላይ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ ባለድርሻ አካላት አስተያየታችሁን ለባለሥልጣኑ በኢሜል አድራሻ consultation@eca.et መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን

DRAFT CONSUMER RIGHTS AND PROTECTION CODE OF CONDUCT-AMH